by Dawit Atreso
ዛሬም በቄለም ወለጋ ለምለም ቀበሌ በተፈፀመ ጥቃት በርካታ ሰዎች ተጨፍጭፈዋል። እሱና ቤተሰቦቹ በአካባቢው ነዋሪ የሆኑ አንድ ነዋሪ እንደገለፀው ዛሬ የተፈፀመው ጭፍጨፋ እጅግ በጣም አሳዛኝ እንደነበር ገልፆ በርካታ ሰው ተገድላል፤ ሴቶች እና ህፃናትም ይገኙበታል ብሏል። በአካባቢው ኔትዎርክ ይሰራ ነበር አሁን ላይ እየሰራ አይደለም ቤተሰቦቼ ቦታው ላይ ነበሩ አምልጠው ማቻራ የምትባል አካባቢ ገብተዋል ፤ ሲል ገልጿል። ጥቃቱን እስካሁን የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር አረጋግጠዋል ፤ " ጨፍጫፊዎቹ የሸኔ ቡድን " ናቸው ብለዋል።
ከጥቂት ቀናት በፊት በምዕራብ ወለጋ ቶሌ ቀበሌ መንግስት በይፋ ባመነው ብቻ ከ300 በላይ ሰዎች መጨፍጨፋቸው ይታወሳል። በወቅቱ ተገድለው የተቀበሩ በአንድ አካባቢ ብቻ እስከ 1500 እንደሚደርስ ቤተስቦቻቸው እዛው ያሉ ነዋሪዎች መናገራቸው አይዘነጋም። አንዳድን ተቋማት ቁጥሩን ከዚህም ከፍ ያደርጉታል። አሁንም ንፁሃን ፣ ምንም ስለፖለቲካ የማያውቁ ህፃናት፣ ሴቶች እየተገደሉ ሲሆን ከቀናት በፊት የነበረው የንፁሃን ጭፍጨፋ ሰሞነኛ አጀንዳ ሆኖ አልፎ ነበር
መብራት እንኳን በቅጡ የሌለው አካባቢ ነው። ከቦቀሎ እና ማሽላ እንጀራ በዘለለ የማይበላ ፤ በኑሮው የተጎሳቆለ ማህበረሰብ ነው እንኳን ጥይት እና ገጀራ ሊገባው ! እጅግ ምስኪን ማህበረሰብ ነው ። ሰው ወዳድ ናቸው ፤ እንግዳም ተቀባይ ናቸው ፤ ያላቸውን አውጥተው የሚያስተናግዱ ናቸው። ፍርድ ከላይ ነው ፤ ፍርድ ከአላህ ነው ለዛ ማህበረሰብ ይሄ አይገባውም ነበር። በሚያሳዝን ሁኔታን የማህበረሰቡን ሮሮ፣ ጩኸት ማን እንደሚሰማው አናውቅም። ጥቃት አድራሾቹን ማን ሃይ እንደሚላቸውም አናቅም። ለማን አቤት እንደምንል ግራ የሚገባ ነው። ለሁለተኛ ጊዜ መሆኑ ነው ባለፈው ከፍ ብሎ ጊምቢ አካባቢ በጣም ብዙ ሰው በተሰመሳሳይ ሁኔታ ተጨፍጭፏል።