by Dawit Atreso
የምሥራቅ አፍሪካ አገራት በአስርት ዓመታት ውስጥ ታይቶ የማይታወቅ ከፍተኛ የኑሮ ውድነት እንደተጋረጠባቸው የዓለም ባንክ ከሰሞኑ አስታውቋል። የሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነት እንዲሁም የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ጫና ተደማምሮ አንዳንድ አገራት ከፍተኛ የኢኮኖሚ ድቀት እያጋጠማቸው መሆኑን ባንኩ ገልጿል። ከዚህም ጋር ተያይዞ ዓመታዊ ትንበያውን ቀንሷል።
ባንኩ በተለይም የምሥራቅ አፍሪካ አገራት እና አንዳንድ የአውሮፓ ክፍሎች ተጎጂ ሆነዋል ብሏል። ከፍተኛ የዋጋ ግሽበት እና ዝቅተኛ የምጣኔ ሀብረት ዕድገት ጥምረት ከ1970ዎቹ ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ ሊመለስ እንደሚችልም ጠቁሟል። አገራቱ በምግብ እና በነዳጅ ዋጋ መጨመር ምክንያት ቀውስ እያጋጠማቸው መሆኑም ተገልጿል። የዓለም ባንክ ኃላፊ ዴቪድ ማልፓስስ ከቢቢሲ ጋር ባደረጉት ቆይታ የቀውሱን ሌላ ጎን ማየት ከባድ ነው ብለዋል። አንዳንድ በማደግ ላይ ያሉ አገራት መንግሥታት እቃዎችን መግዛት አለመቻላቸውን እንዲሁም የብድር ዕዳ ውስጥ እየተዘፈቁ ነው ብለዋል ። የባንኩ አዲስ የዓለም አቀፍ እድገት ትንበያ ከዜሮ በታች 2.9 በመቶ ሲሆን፣ ይህም በ80 ዓመታት ውስጥ ከፍተኛው መቀነስ የታየበት መሆኑን ቢቢሲ አስነብቧል።
by Dawit Atreso
#ደቡብ_አፍሪካ | " በ3 ወራት በትንሹ 6,000 ሰዎች ተገድለዋል " ከፍተኛ የሆነ የወንጀል ድርጊቶች ይፈፀምባቸዋል ተብለው ከሚጠሩ ሀገራት አንዷ ደቡብ አፍሪካ ናት። ከፖሊስ በወጣ ሪፖርት መሰረት በሀገሪቱ በሶስት ወራት በትንሹ 6,000 ሰዎች ተገድለዋል። በጥር እና መጋቢት መካከል 6,083 ሰዎች የተገደሉ ሲሆን ካለፈው አመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር (4,976 ነበር) የ22.2 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል። ከግድያ በተጨማሪ የፆታዊ ጥቃት ጋር በተያያዘ የተፈፀሙ ወንጀሎች በ13.7 በመቶ ከፍ ያለ ሲሆን 10,818 ሰዎች ተደፍረዋል። እገታ እና አፈናም በከፍተኛ ሁኔታ የጨመረ ሲሆን 3,306 ኬዞች ሪፖርት ተደርጓል ፤ ይህም ከአንድ አመት በፊት ከነበረው በእጥፍ ይበልጣል ተብሏል። የሀገሪቱ ፖሊስ " የዚህ አመት የመጀመሪያዎቹ 3 ወራት ጨካኔ የተሞላበት እና ለብዙ ደቡብ አፍሪካውያን ደህንነታቸው ያልተጠበቀ ነበር " ብሏል። " ብቻዬን ከሚሰሩ ወንጀሎች ጋር ተፋልሜ ላሸንፍ አልችልም " ያለው የደቡብ አፍሪካ ፖሊስ " ከማህበረሰቡ ጋር በጠንካራ እምነት ላይ የተገነባ ጥልቅ አጋርነት ያስፈልገኛል " ሲል ገልጿል።