ጥቃት አድራሾቹ የታጠቁት መሳርያ እና ድጋሚ በአማርኛ ተናጋሪዎች ላይ ጭፍጨፋ !

 ethiopian human right commussion

ከሟቾች መካከል ሴቶች እና ህፃናት ይገኙበታል

05 July 2022

by Dawit Atreso

ዛሬም በቄለም ወለጋ ለምለም ቀበሌ በተፈፀመ ጥቃት በርካታ ሰዎች ተጨፍጭፈዋል። እሱና ቤተሰቦቹ በአካባቢው ነዋሪ የሆኑ አንድ ነዋሪ እንደገለፀው ዛሬ የተፈፀመው ጭፍጨፋ እጅግ በጣም አሳዛኝ እንደነበር ገልፆ በርካታ ሰው ተገድላል፤ ሴቶች እና ህፃናትም ይገኙበታል ብሏል። በአካባቢው ኔትዎርክ ይሰራ ነበር አሁን ላይ እየሰራ አይደለም ቤተሰቦቼ ቦታው ላይ ነበሩ አምልጠው ማቻራ የምትባል አካባቢ ገብተዋል ፤ ሲል ገልጿል። ጥቃቱን እስካሁን የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር አረጋግጠዋል ፤ " ጨፍጫፊዎቹ የሸኔ ቡድን " ናቸው ብለዋል።

ከጥቂት ቀናት በፊት በምዕራብ ወለጋ ቶሌ ቀበሌ መንግስት በይፋ ባመነው ብቻ ከ300 በላይ ሰዎች መጨፍጨፋቸው ይታወሳል። በወቅቱ ተገድለው የተቀበሩ በአንድ አካባቢ ብቻ እስከ 1500 እንደሚደርስ ቤተስቦቻቸው እዛው ያሉ ነዋሪዎች መናገራቸው አይዘነጋም። አንዳድን ተቋማት ቁጥሩን ከዚህም ከፍ ያደርጉታል። አሁንም ንፁሃን ፣ ምንም ስለፖለቲካ የማያውቁ ህፃናት፣ ሴቶች እየተገደሉ ሲሆን ከቀናት በፊት የነበረው የንፁሃን ጭፍጨፋ ሰሞነኛ አጀንዳ ሆኖ አልፎ ነበር

መብራት እንኳን በቅጡ የሌለው አካባቢ ነው። ከቦቀሎ እና ማሽላ እንጀራ በዘለለ የማይበላ ፤ በኑሮው የተጎሳቆለ ማህበረሰብ ነው እንኳን ጥይት እና ገጀራ ሊገባው ! እጅግ ምስኪን ማህበረሰብ ነው ። ሰው ወዳድ ናቸው ፤ እንግዳም ተቀባይ ናቸው ፤ ያላቸውን አውጥተው የሚያስተናግዱ ናቸው። ፍርድ ከላይ ነው ፤ ፍርድ ከአላህ ነው ለዛ ማህበረሰብ ይሄ አይገባውም ነበር። በሚያሳዝን ሁኔታን የማህበረሰቡን ሮሮ፣ ጩኸት ማን እንደሚሰማው አናውቅም። ጥቃት አድራሾቹን ማን ሃይ እንደሚላቸውም አናቅም። ለማን አቤት እንደምንል ግራ የሚገባ ነው። ለሁለተኛ ጊዜ መሆኑ ነው ባለፈው ከፍ ብሎ ጊምቢ አካባቢ በጣም ብዙ ሰው በተሰመሳሳይ ሁኔታ ተጨፍጭፏል።




ጋዜጠኛው በድጋሚ መታፈኑ!

 ethiopian human right commussion
02 July 2022

by Dawit Atreso

ከቀናት በፊት ሲቪል በለበሱ ሰዎች ከቤቱ የተወሰደው ጋዜጠኛ ያየሰው ሽመልስ እስካሁን ያለበትን ማወቅ እንዳልቻሉ ቤተሰቦቹ ገለፁ። ቤተሰቦቹ ዛሬ በላኩልን መልዕክት ሰኔ 21 ቀን 2014 ዓ/ም 7 ሲቪል የለበሱ ሰዎች ከቤቱ ከወሰዱት በኃላ እስካሁን ድረስ ያለበትን ለማወቅ እንዳልቻሉ አስረድተዋል። " ፌዴራል ፖሊስ እና አዲስ አበባ ፖሊስ ብንፈልገውም ልናገኘው አልቻልም ፤ ለኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ብናመለክትም ከፌዴራል ፖሊስ እና አዲስ አበባ ፖሊስ ውጭ እንደሆኑ ነው የነገረን " ሲል አሳውቆናል ሲሉ ገልፀዋል። ቤተሰቦች በያየሰው ሽመልስ ቦታ አለመታወቅ ከፍተኛ ጭንቀት ላይ መሆናቸውን ገልፀው የወሰዳቸው አካል ያለበትን ብቻ እንዲያሳውቃቸው ተማፅነዋል።

ጋዜጠኛ ያየሰው ከጥቂት ቀናት በፊት ነበር በ10 ሺ ብር ዋስ ፍርድ ቤት ከእስር እንዲለቀቅ ወስኖለት የተለቀቀው። ከዚህ በኃላ ነው በድጋሚ የተያዘው። በተመሳሳይ ጋዜጠኛ ያየሰው ሽመልስ በተወሰደ ከአንድ ቀን በኃላ ጋዜጠኛ አበበ ባዩ ምሽት 4:30 ሲቪል በለበሱ ሰዎች የተወሰደ ሲሆን ቤተሰቦቹ እሱንም እካሁን ማግኘት እንዳልቻሉ አመልክተዋል። ፌዴራል ፖሊስ እና አ/አ ፖሊስ መጠየቃቸውን ነገር ግን እንዳላገኙት ፤ ያለበትን ለማወቅም ለኢሰመኮ ቢያመለክቱም ያለበትን ለማግኘት እንዳልተቻለ ገልፀዋል። የአበበ ባዩ ቤተሰቦችም ጭንቀት ላይ መሆናቸውን ገልፀው የወሰዳቸው አካል ያለበትን ቦታ እንዲያሳውቃቸው ተማፅነዋል። ጋዜጠኛ አበበ ባዩ ከጥቂት ወራት በፊት ለእስር ተዳርጎ መፈታቱ የሚታወስ ነው።


የሱዳን መንግስትና የአፋኙ የኢትዮጵያ መንግስት ጦርነት እየጎሰሙ ነው!!

 ethiopian human right commussion
27 June 2022

by Dawit Atreso

በዛሬው እለት ሱዳን ኢትዮጵያን በግልፅ መውረር ጀምራለች፤ ባትጀምር ይግርመኝ ነበር። አይ ኢትዮጵያ! የአራት ኪሎው ተረኛው መንግስት አሁን ላይ በተለይም የኢትዮጵያን ህዝብ ለማደንዘዝ እና አጀንዳ ለማስቀየር የተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ሌት ተቀን በመስራት ላይ ይገኛል። ይንንም ተከትሎ በወልጋ ሆን ብሎ ያስጨፈጨፋቸውን ከሁለት ሺህ በላይ ንፁሃን አማርኛ ተናጋሪ ከህጻን እስከ አዋቂ ነፍሶችን፤ አሁን ደግሞ በሱዳን እና በደቡብ ሱዳን ተወረናል ድረሱልን እያለ ይገኛል። ግልጹን እንነጋገር ከተባለ የዘሪፖርተር ጋዜጣ በአዲሱ በደቡብ ምዕራብ ክልል የደቡብ ሱዳን ታጣቂዎች ከመቶ ሃምሳ በላይ ኪሎ ሜትር በላይ መሬት መውረራችውን ገልጾ ሲያበቃ በሰአታት ውስጥ ከዌብሳይቱ ላይ ዘገባውን እንዲያወርድ ተደርጓል። አይ አፋኙ !!

የሱዳን መንግስትና የአፋኙ የእትዮጵያ መንግስት ጦርነት እየጎሰሙ የሚገኙበት ሁኔታ ነው ያለው። በዚህም የሱዳኑ መሪ አልቡርሃን የሃገሩን ህዝብ አጀንዳ ለማስቀየር እና ካለበት ተቃውሞ ራሱን ለማዳን በማለት የጦርነት ጉሰማ ላይ ይገኛል። በአንፃሩ ለኢትዮጵያው መንግስት የተመችው ሁኔታ ተፈጥሮለታል። የንፁሃን ደም በከንቱ እየፈሰሰ እና ሰብአዊ መብት እና በአንድ ሃገር ላይ አንደኛ ዜጋ እና ሁለተኛ ዜጋ ሆኖ በተከፋፈለበት ሁኔታ አሁን ድጋሚ ወደ ጦርነት ለመግባት የሚደረግ ጉሰማ ተገቢ ኣይደለም።

በምዕራብ ጎንደር ዞን የምዕራብ አርማጨሆ ወረዳ አስተዳዳሪ የሆኑት አቶ ደሳለኝ አያና ለቢቢሲ አማርኛ አገልግሎት የሰጡት ቃል ፦

- የሱዳን ሠራዊት በኢትዮጵያ በኩል ያሉ የድንበር አካባቢዎችን በከባድ መሳሪያ ደብድቧል። ድብደባው ለቀናት የዘለቀ ነው። እስከ ትላንት ማክሰኞ ከሰዓት ድረስ ሲደበድቡ ነበር።

- ነዋሪዎች ግጭቱ ሊባባስ ይችላል የሚል ስጋት አላቸው። አንዳንዶችም በአቅራቢያ ወዳሉ አካባቢዎች የመሄድ ሃሳብ አላቸው።

- ባለፉት ሶስት ቀናት በተፈጸመው የከባድ መሳሪያ ጥቃት #በሰው_ላይ_ጉዳት_አልደረሰም። የከባድ መሳሪያዎቹ በእርሻ ቦታዎችና የግብርና ካምፖች ላይ ጉዳት አድርሰዋል።

- በሱዳን የከባድ መሳሪያ ጥቃት ምክንያት ነዋሪዎች ባለፉት ቀናት በእርሻ ማሳቸው ላይ የተለመደውን የዕለት ከዕለት ሥራቸውን ከማከናወን ተቆጥበዋል።

- የንግድና የሥራ እንቅስቃሴ ተስተጓግሏል። ሱዳንና ኢትዮጵያ የሚገናኙበት የድንበር ከተማ የሆነችው የገለባት መተላለፊያ #ተዘግቷል።

ፓርላማውና የአብይ አህመድ ስላቅ!!!

Jawar mohamed
June 15 2022

በጋዜጣዉ voice|ET News by Dawit Atreso

የአብይን ንግግር ታግሶ መስማት በጣም አታካች ነው።ከተለመደው ውጪ ምን ሊያስተላልፍ ይችላል ማለት ተገቢ ጥያቄ ቢሆንም ነገር ግን ምንም የተለየ ነገር አልተናገረም። በ 2013 ከተከፈተው የትግራይ ህዝብን ማውደም ዘመቻ እና ኢትዮጵያ የምትባል ሃገርን በተጠና መንገድ ለማፍረስ የኦሮሞው መንግስት ከጀምረ ሰነባብቷል። በተለይም የኢትዮጵያን ሰሜንን ክፍል 30 ዓመት ውደ ኋላ በመመልስ ለወደፊቷ ኦሮሚያ ሌት ተቀን በመስራት ላይ ይገኛል። ለዚህም ይመስላል በተቃዋሚ ተርታ የምናውቃቸው አንድ አንድ ፖለቲከኞች አብይን በይፋ መደገፍ የጀመሩት ።

ከምንጫችን እንደተረዳነው በዚህ አራት አመት ውስጥ ብቻ ከ 1400 በላይ ምልምሎችን ከኦሮሚያ ክልል በመምረጥ የደህንነት ስልጠና እንዲያገኙ አድርገዋል። ይገርማል!! ጠቅላይ ሚንስትሩ በፓርላማው ከተናገሩት መካከል በአማራ ክልል እና በትግራይ ክልሎች መካከል ስለሚደረገው ድርድር እና የወልቃይት ውዝግብ ጥያቄ በአቶ ደሳለኝ ጫኔ ሲቀረበላቸው፤ የመለሱት የነበረው የእሳቸው ሃላፊነት እንዳልሆነ በመግለፅ አቶ ደመቀ መኮንን እንዳሉበት ተናግረዋል ።

ጠቅላይ ሚንስትሩ በተጨማሪም የአዲስ አበባ ህዝብ ላይ የዘረኝነት ቦንብ ጥለው ውርደዋል። ከተናገሩት ውስጥ በሰሞኑ በይፋ ለወጣው መረጃ ማለትም በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ባሉ ትምህርት ቤቶች ውስጥ የኦሮሚያ ብሄራዊ መዝሙር በክፍለ ከተማው አስተዳደር በሚደገፍ መልኩ ተማሪዎች እንዲዘምሩ መደረጋቸውን፤ የውጪ ሃገራት ትምህርት ቤቶች በከተማዋ ብሄራዊ መዝሙራችውን እንደሚያዘምሩ ገለፀው የኦሮምኛ ቋንቋ በህገወጥ መንገድም ቢሆን ቢዘመር ግድ እንደማይሰጣችው ተናግረዋል።

ስለምትከታተሉን እናመሰግናለን!!!!!

በጋምቤላ ከተማ ረፋዱን የተኩስ ልውውጥ እንደነበር ተነገረ

Jawar mohamed
14 June 2022

በጋዜጣዉ voice|ET News by Dawit Tesfaye

በጋምቤላ ክልል መቀመጫ ጋምቤላ ከተማ በታጣቂዎች እና በጸጥታ ኃይሎች መካከል ዛሬ ማክሰኞ ንጋት አካባቢ የጀመረ ውጊያ ሲካሄድ መቆየቱን የሚያመለክቱ መረጃዎች ወጥተዋል፡፡ የክልሉ ፕሬስ ሴክሪተሪያት ጽሕፈት ቤት ባወጣው መረጃ የጋምቤላ ነጻነት ግንባር እና የሸኔ ወታደሮች በጋራ ተኩስ መክፈታቸውን ገልጧል፡፡

መንግሥት በሽብርተኝነት የሰየመውና ሸኔ ሲል የሚለው ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ሲል የሚጠራው ኃይል የሕዝብ ግንኙነት ነው የሚባለው ኦዳ ተርቢ የተሰኘው ግለሰብ በበኩሉ በትዊተር ገጹ ሠራዊታቸው ከጋምቤላ ነጻነት ግንባር ጋር በመሆን በጋምቤላ ከተማ ወታደራዊ ዘመቻ እያካሄደ መሆኑን ገልጿል።ግለሰቡ አክሎም ከጋምቤላ በተጨማሪም በምዕራብ ኦሮሚያ በደምቢ ዶሎ ተመሳሳይ ወታደራዊ ዘመቻ እያደረገ መሆኑን ገልጿል። ቢቢሲ አንድ ሥማቸው ያልተገለጸ የክልሉን ከፍተኛ ባለሥልጣን ጠቅሶ እንደዘገበው፤ ክስተቱ በጋምቤላ ከተማ ውስጥ ማጋጠሙን አረጋግጠው፣ በዚህም የሰው ህይወት መጥፋቱንና የተጎዱ መኖራቸውን ገልጸዋል። ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉት የክልሉ ባለሥልጣን ቢያንስ ሁለት የፀጥታ ኃይሎች እንዲሁም ከታጣቂዎቹ የሦስቱ ህይወት ማለፉን ከሆስፒታል ምንጮቻቸው መረዳታቸውን ተናግረዋል።

"…አጀንዳህን አትቀይር…!!

Jawar mohamed
27 May 2022

በጋዜጣዉ voice|ET News by Dawit Atreso

"…የኦፌኮው ምክትል ሊቀ መንበር ሃጂ ጀዋር መሀመድ 30k ተመልካች በነበረው ከአቡንቱ ዩቲዩብ ቻናል ጋር ያደረገውን ቃለ መጠይቅ ደግሜ አየሁት። የጃዋር እርጋታው፣ ጥንቃቄው፣ የድምጽ ቶኑ ዝግታ፣ መወራጨት፣ መጮሁ፣ መሳለቁ፣ ማሳቀቁ፣ ማላገጡ፣ መተንኮስ ማንጓጠጡ ሁሉ ቀርቶ እንዲህ ጭጭት ብሎ ሰውነቱ ትንሽ ከስቶ፣ ፀጉሩም ሸብቶ፣ ለሃገር ሰላም ሁሉም ይጸልይ የሚል ሐዋርያ መስሎ መታየቱን ታዝቤአለሁ። እስር እንዲህ የሚያርቅ ከሆነ እስር ለዘላለም ይኑር። ትንሽ ቢቆይ ደበበ እሸቱን ወይም አንዷለም አራጌን ይሆን ነበር የሚሉም ሰዎች ተደምጠዋል። ፐ እርጋታ…!
"…ከወር በፊት በኦፌኮ በፖለቲካ ድርጅቱ በኩል " ጽንፈኛ" ብሎ የከሰሰውን ፋኖንም በተመለከተ አሁን የሰነዘራቸው መልእክቶች ሰማይና ምድር ሆኖ አግኝቻለሁ። በዚህ አጭር ጊዜ ውስጥ የፋኖ አዛኝ፣ የዐማራን ብሔርተኝነት መጦዝና፣ መመንጠቅ እንደሚያሳስበው ሆኖ መቅረቡም ገርሞኛል።
"…ጃዋር በዚህ ቃለ መጠይቁ የዐማራ ፖለቲካ የማይታመንና ፈጣን የሆን የለውጥ ሁኔታ ውስጥ መግባቱን፣ ብሔርተኝነቱም ፈጣን የሆነ እድገት ማሳየቱን፣ በተለይ የፌደራል መንግሥቱ ከህወሓት ጋር በነበረው ጦርነት ወቅት የዐማራን ድጋፍ መፈለጉን ተከትሎ ዐማራን በሙሉ ወታደር ማድረጉን፣ መሳሪያ ማርክና ታጠቅ ብሎም ሁሉም በአንዳፍ ብሎ መታጠቁን ሳይደብቅ መስክሯል። እንዲህ ካልከው በኋላ መልሰህ በኃይል መሳሪያህን እገፍሃለሁ መባሉ አደጋ መሆኑን በሰከነ መንፈስ ሲናገር ተደምጧል።
"…የፌደራል መንሥቱ ከህወሓት ጋር ሲደራደር ዐማራን በድርድሩ አለመሳተፉ፣ የመገለልና የመገፋት ስሜት መፈጠሩን፣ ለጦርነቱ ሕይወቱን እንዲገብር ጠርተኸው፣ የማረከውን መሳሪያ ለግልህ ውስድ ብለኸው ስታበቃ መልሰህ የድርድሩ ተሳታፊ ሳታደርገው ውሰድ ያልከውንም ትጥቅ በጉልበት ፍታ ማለቱ ከባድ አደጋ እንዳለውም ጃዋር በለሆሳስ ምክር ሲሰጥ ታይቷል።
"…ፋኖ ላይ የሰላ ትችት ማድረግ ይቻላል ይላል ጃዋር። (እሱ በድርጅቱ በኩል ጽንፈኛው ፋኖ ሲል እንደነበረው ማለት ነው) ነገር ግን ፋኖን በማግለልና በማሳደድ አክራሪወች ቢኖሩም እንኳ እደመስሳቸዋለሁ፣ አወድማቸዋለሁ በሚል መንግሥታዊ ጉልበተኛ አስተሳሰብ አይደለም ብሏል። ፋኖነትን ለጊዜው እናስተፍሰው ይሆናል ነገር ግን የፋኖነትን ስሜት ይበልጥ ታሳድገዋለህ እንጂ በዚህ መልኩ ልታሸንፈው አትችልም ነው ያለው ጃዋር። ( ህወሓት ዱላ፣ በትር ሳይቀር በእጁ እንዳይዝ አድርጋ ረግጣ የያዘችውን ዐማራ በዐዋጅ ታጠቅ ካልከው በኋላ ድንገት መጥተህ ፍታ ስትለው አደጋ አለው የሚል ነው የሚመስለው ጃዌ)
"…እርግጥ ነው መንግሥት በፋኖ ላይ የወሰደው አሳፋሪ ተግባር መልሶ እየለበለበው ነው። ከወር በፊት ጽንፈኛው ፋኖ እርምጃ ይወሰድበት እያለ መንግሥትን ሲማጸን፣ ሲገፋ የነበረው ጃዋርስ ምን ዓይነት ራዕይ ታይቶት ነው ይሄ ነገር አደገኛ ነው ይቁም ወደሚል ድንገቴ ሰበካ የወረደው። ፋኖ የገደለው ሰውም፣ የዘረፈውም ባንክ እንደሌለ እየታወቀ ስሙ ሲያጠለሹ ከከረሙ በኋላ አሁን ደርሰው አዛኝ መስለው መከሰታቸው ጥያቄ ይጭራል።
"…እኔ ግን እላለሁ ዐማራ አሁንም በሰበካ፣ በኢትዮጵያ ሱሴ ዲስኩር ለዳግም ንቀት፣ ለዳግም ሞትና ስደት እንዳትዳረግ፣ እንደ ዜጋ እንድትታይ፣ እንድትከበር ፋኖነትህን አጥብቅ። የሰላምን በር አትዝጋ፣ ግን ባዶ እጅህን አይሁን። ሰዎቹ የሚታመኑ አይደሉምና እየተፈራረቁ በተበረጠቁ ቁጥር አጀንዳህን አትቀይር። ጃዋር ግን ሲታይ እንደለማ መገርሳ፣ እንደ ዐቢይ አሕመድ ሲመሽ ካላደፈረሰው በቀር ለአሁኑ ሲታይ እጅግ ያደገ፣ የተረጋጋ፣ እንደ አረጋዊ የሰከነ መስሎ ለመተወን ሞክሯል።
"…የአሜሪካንን ፓስፖርት ከማግኘት 3 ወር ነው የፈጀብኝ፣ የኢትዮጵያ ፓስፖርት ለማግኘት 2 ዓመት እንደፈጀበት የተናገረው ስሰማ ግን የኢትዮጵያዊነትን ክቡርነትና ውድ ማንነት ሲመሰክር ማየቴን አልደብቅም። ኢትዮጵያ የናቋት፣ የሰደቧት፣ የረገሟት፣ ሰድበውም ለሰዳቢ አሳልፈው የሰጧት ኃይሎች በሙሉ እግሯ ላይ ይወድቃሉ። "…ፋኖም ዐማራም አጀንዳችሁን አትቀይሩ…!!

ከቤታቸው እንደወጡ ያልተመለሱት የብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ ማሞ ቤተሰቦች ጭንቀት ውስጥ እንደገቡ ተናገሩ

asamnew tsige
27 May 2022

በጋዜጣዉ voice|ET News by Dawit Atreso

ብርጋዴር ተፈራ ማሞ ከትናንት በስቲያ ግንቦት 8 ቀን 2014 ዓ.ም. ረፋድ ላይ ከቤታቸው እንደወጡ ሳይመለሱ መቅረታቸው፣ ከፍተኛ ሥጋትና ጭንቀት እንዳደረባቸው ባለቤታቸው ለሪፖተር ተናገሩ፡፡ ባለቤታቸው ወ/ሮ መነን ኃይሌ እንደገለጹት፣ ባለቤታቸው የሚኖሩት በባህር ዳር ከተማ ነው፡፡ አዲስ አበባ የመጡት ሰሞኑን ሲሆን፣ በሰውነታቸው ውስጥ ያለውን ጥይት (በኢሕአዴግ ዘመነ መንግሥት በውጊያ ላይ እያሉ በሰውነታቸው ውስጥ ገብተው ያልወጡ ጥይቶች)ን በሚመለከት ሐኪም ለማነጋገርና ለመታከም፣ እንዲሁም አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተመደበ ልጃቸውን አስመዝግበው ለመመለስ ነበር፡፡ ብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ ሰኞ ግንቦት 8 ቀን 2014 ዓ.ም. ከጠዋቱ 5፡00 ሰዓት አካባቢ አቶ ዮሐንስ ቧያለውን ለማግኘት ከቤታቸው እንደወጡ የተናገሩት ወ/ሮ መነን፣ ‹‹10፡00 ሰዓት አካባቢ ስልክ ብደውልለት ሊያነሳልኝ አልቻለም፤›› ብለዋል፡፡ የባለቤታቸው ስልክ ቢጠራም ሊያነሱ ስላልቻሉ ለአቶ ዮሐንስ መደወላቸውን የተናገሩት ወ/ሮ መነን፣ ከአቶ ዮሐንስ ያገኙት ምላሽ ግን አብረው ቆይተው መለያየታቸውን ብቻ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ እስከ ትናንትና ግንቦት 9 ቀን 2014 ዓ.ም. ከንጋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ የባለቤታቸው ስልክ ሲሠራ ቆይቶ እንደተዘጋም አክለዋል፡፡

ኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) አመራር የሆነት ኮነሌል ገመቹ አያና ከስር እንዲለቀቁ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት 3ኛ ሰበር ሰሚ ችሎት ወሰነ

image here
16 May 2022

በጋዜጣዉ voice|ET News by Dawit Atreso


የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) አመራር የሆነት ኮነሌል ገመቹ አያና ከስር እንዲለቀቁ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት 3ኛ ሰበር ሰሚ ችሎት ወሰነ። ኮነሌል ገመቹ አያና በግንቦት 9 ቀን 2014 ዓ/ም በተከሰሱበት በሽብር ወንጀል በከፍተኛው ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 3ኛ የፀረሽብርና የህገመንግክት ጉዳዮች ወንጀል ችሎች በነጻ ከተሰናበቱ በኋላ በነጋታው ከቂሊንጦ ማረሚያ ቤት በር ላይ ሲወጡ በኦሮሚያ ፖሊስ ተይዘው ለ6 ወር በገላን ፓሊስ ጣቢያና በወታደራዊ ካንፕ እንዲሁም በአዋሽ መልካሳ በአንድ ጀነራል ዶሮ እርባታ ውስጥ ታስረው እንደነበርና ከህዳር 16 ጀምሮ ደግሞ በፌደራል ፖሊስ በስር ላይ እንደነበሩ ለፍርድ ቤት አስረድተው ነበር። ኮነሌል ገመቹ አያናን በአደራ ከመቀበል ውጪ ምንም የወንጀል የምርመራ መዝገብ እንዳልተከፈተበት የፌደራል ፖሊስ ቀርቦ ማብራሪያ መስጠቱንም ይታወሳል።

ሰበር ሰሚ ችሎቱ የኦሮሚያ ፖሊስ ቀርቦ የኮነሌል ገመቹ የእስራት ሁኔታን እንዲያስረዳ ታዞ የነበረ ሲሆን ትላንት በነበረ ቀጠሮ ችሎት አልቀረበም። ይህን ተከትሎ መርምሮ ትዛዝ ለመስጠት ችሎቱ ለዛሬ በይደረሰ ቀጥሮ የነበረ ሲሆን መርምሮ ኮነሌል ገመቹ አያና ከስር እንዲፈቱ ወስኗል።

የተመረጡ ርዕሶች