by Dawit Atreso
ዛሬም በቄለም ወለጋ ለምለም ቀበሌ በተፈፀመ ጥቃት በርካታ ሰዎች ተጨፍጭፈዋል። እሱና ቤተሰቦቹ በአካባቢው ነዋሪ የሆኑ አንድ ነዋሪ እንደገለፀው ዛሬ የተፈፀመው ጭፍጨፋ እጅግ በጣም አሳዛኝ እንደነበር ገልፆ በርካታ ሰው ተገድላል፤ ሴቶች እና ህፃናትም ይገኙበታል ብሏል። በአካባቢው ኔትዎርክ ይሰራ ነበር አሁን ላይ እየሰራ አይደለም ቤተሰቦቼ ቦታው ላይ ነበሩ አምልጠው ማቻራ የምትባል አካባቢ ገብተዋል ፤ ሲል ገልጿል። ጥቃቱን እስካሁን የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር አረጋግጠዋል ፤ " ጨፍጫፊዎቹ የሸኔ ቡድን " ናቸው ብለዋል።
ከጥቂት ቀናት በፊት በምዕራብ ወለጋ ቶሌ ቀበሌ መንግስት በይፋ ባመነው ብቻ ከ300 በላይ ሰዎች መጨፍጨፋቸው ይታወሳል። በወቅቱ ተገድለው የተቀበሩ በአንድ አካባቢ ብቻ እስከ 1500 እንደሚደርስ ቤተስቦቻቸው እዛው ያሉ ነዋሪዎች መናገራቸው አይዘነጋም። አንዳድን ተቋማት ቁጥሩን ከዚህም ከፍ ያደርጉታል። አሁንም ንፁሃን ፣ ምንም ስለፖለቲካ የማያውቁ ህፃናት፣ ሴቶች እየተገደሉ ሲሆን ከቀናት በፊት የነበረው የንፁሃን ጭፍጨፋ ሰሞነኛ አጀንዳ ሆኖ አልፎ ነበር
መብራት እንኳን በቅጡ የሌለው አካባቢ ነው። ከቦቀሎ እና ማሽላ እንጀራ በዘለለ የማይበላ ፤ በኑሮው የተጎሳቆለ ማህበረሰብ ነው እንኳን ጥይት እና ገጀራ ሊገባው ! እጅግ ምስኪን ማህበረሰብ ነው ። ሰው ወዳድ ናቸው ፤ እንግዳም ተቀባይ ናቸው ፤ ያላቸውን አውጥተው የሚያስተናግዱ ናቸው። ፍርድ ከላይ ነው ፤ ፍርድ ከአላህ ነው ለዛ ማህበረሰብ ይሄ አይገባውም ነበር። በሚያሳዝን ሁኔታን የማህበረሰቡን ሮሮ፣ ጩኸት ማን እንደሚሰማው አናውቅም። ጥቃት አድራሾቹን ማን ሃይ እንደሚላቸውም አናቅም። ለማን አቤት እንደምንል ግራ የሚገባ ነው። ለሁለተኛ ጊዜ መሆኑ ነው ባለፈው ከፍ ብሎ ጊምቢ አካባቢ በጣም ብዙ ሰው በተሰመሳሳይ ሁኔታ ተጨፍጭፏል።
by Dawit Tesfaye
"ፈጣሪዬን ጠየኩት ለምን እኔን አተረፍከኝ ብዬ" ይህን ልብ የሚነካ ንግግር የተናገሩት 32 ቤተሰባቸውን በዘረኛው እና በ ብልፅግና ፓርቲ በቀጥታ በሚደገፈው በኦነግ ታጣቂ ጭፍጨፋ ያጡት ሰው ናቸው። በተለይም ይህ አማራን እና አማርኛ ተናጋሪ ጠልነት በይፋ ከ4 ዓመታት በፊት በግልፅ በጥላቻ እና በሀገሪቱ በይፋ ለተንሰራፋው ሁሉን አቀፍ ተረኝነት መታያ ሆኗል። በተለይም ዘረኛው አብይ አህመድ በቀጥታ ስርጭት በፓርላማው በይፋ የዘረኝነት ቅስቀሳ እና የጥላቻ ቅስቀሳ ንግግር በማድረግ ላይ ይገኛል።
ይህንንም ከሚያረጋግጡት ማስረጃዎች አንዱ ድግሞ ዘረኛው ጠቅላይ ሚንስትር በኦሮሚያ ክልል በምክትል ፕሬዝዳንትነት ሲራ የተናገረው አሁን ላይ አፍትልኮ በመውጣት ላይ ይገኛል። በዚያን ወቅት ከተናገረው ውስጥ የ ኦሮሞ ህዝብ መሬትን ለሌላው ብሄር መሸጥ እንደሌለበት እና የመሬትን ጉዳይ በተቻለ አቅም ችላ እንዳይሉት ሲያሳስብ ተደምጧል። ይህ ንግግር በስልጣን ላይ በወጣበት ወቅት ለኢትዮጵያ ህዝብ ቃል ከገባውና አንድነትን ከሰበከበት ጋር የተራራቀ ነው። በተለይም በዚህ ወቅት ኢትዮጵያ ለገባችበት ውጥንቅጥ በቀጥታ ተጠያቂ የሚሆነው አካል የኦሮሞው መንግስትና መሪው ናቸው።
ታድያ የጠቅላዩን ትእዛዝ በቀጥታ በመቀበል በ ወለጋ ጊምቢ በከፋ ሁኔታ ከ 1 ወር ህፃን እስከ 100 ዓመት አዛውንት በመንግስት ተቀጣሪ አነግ ታጣቂዎች በአሰቃቂ ሁኔታ ተጨፍጨፈዋል። በጭፍጨፋው ወቅት በስፍራው ከነበሩት እና ካመለጡት ሰው ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለክተው በወቅቱ መከላከያ በወጣበት ቅስፈት ነው መተው ጭፍጨፋውን የጀመሩት ብለዋል። አክለውም ወዲያው የስልክ እና ኢንተርኔት አገልግሎት መቋረጡን ገልፀዋል።
by Dawit Atreso
የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ከእስር እንዲፈታ ወይም የማይፈታበትን ምክንያት ካለ ችሎት ቀርቦ እንዲያስረዳ ታዞ ነበር።
የታዘዘው ለዛሬ ሀሙስ ሰኔ 30 ሲሆን የፌደራሉ ከፍተኛ ፍ/ቤት 1ኛ ፀረ ሽብር ችሎት ቀርቦ፣ የዋስትናው ብይን በፌደራሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት የታገደ ስለሆነ ሊፈፅም ያለመቻሉን አስረድቷል።
ችሎቱም ያልተፈታበትን ይሄን የጠቅላይ ፍ/ቤት ምክንያት ተቀብሎ አሰናብቶናል።
በዚህ መሠረት ጠቅላይ ፍ/ቤት፣ ዐቃቤ ሕግ ባቀረበው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በዋስትና ሊፈታ አይገባም ክርክር ላይ ይግባኙን ለማድመጥ ለሐምሌ 7 ቀን 2014 ዓ.ም ቀጠሮ መስጠቱን ቤተሰቦቹ ተናግረዋል።
by Dawit Atreso
የ " ፍትህ መጽሔት " ማኔጂግ ዳሪክተር ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ " የሀገር መከላከያ ሰራዊትን በህዝብ ዘንድ አመኔታ ለማሳጣትና ሁከትና ብጥብጥ በማስነሳት ወንጀል " መጠርጠሩን መርማሪ ፖሊስ ዛሬ ለፍ/ቤት ገልጿል።
ፖሊስ ጋዜጠኛ ተመስገን በተጠረጠረበት ሁከትና አመጽ ማስነሳት ወንጀል በምስክር ለማስመረጥና የምስክር ቃል ለመቀበል ተጨማሪ ማስረጃ ለመሰብሰብ እና የምርመራ ስራውን አጠናክሮ ለመቅረብ 14 ተጨማሪ የምርመራ ቀናት እንዲሰጠው ችሎቱን ጠይቋል።
የጋዜጠኛ ተመስገን ጠበቃ ሄኖክ አክሊሉ መከላከያን መተቸት እምነት ማሳጣት አለመሆኑን ጠቅሶ ተከራክሯል።
በምስክር ማስመረጥ ለተባለውም ቢሆን ተመስገን አገር የሚያውቀው በመሆኑ ማስመረጥ ጥያቄው ተገቢ እንዳልሆነ ገልጿል።
ጠበቃው አክሎም ጋዜጠኛ ተመስገን የሚሰራበት ሚዲያ ፍቃድ ያለው ህጋዊ ተቋም እንደመሆኑ ወንጀል ሰራ እንኳ ቢባል በመገናኛ ብዙሃን አዋጅ እንጂ በጊዜ ቀጠሮ ሊጠየቅ እንደማይገባ ተከራክሯል።
ፖሊስ በዩቱዩብ ቃለመጠይቅ እያደረገ ከሌሎች አካላት ጋር ሁከትና አመጽ የማነሳሳት ስራ እየሰሩ ነው ሲል ባቀረበው የመነሻ ምርመራ ሪፖርትን በተመለከተ ጋዜጠኛ ተመስገን ከ4 አመት ወዲህ ምንም አይነት ከማንም ጋር ቃለመጠየቅ እንዳላደረገ ጠበቃ ሄኖክ አብራርቷል።
በሚሰሩበት ሚዲያ የሀገር መከላከያ ተቋምም ቢሆን ተተችቻለው በህዝብ ዘንድ እምነት አጣሁ ብሎ አለመቅረቡን ጠቅሰው ቢቀርብ በመገናኛ ብዙሀን አዋጅ መሰረት በሚሰራበት ሚዲያ ማስተካከያ ከማድረግ እንደማይታለፍ መከራከሪያ ነጥቡ ጠቅሷል።
by Dawit Atreso
ኢትዮጵያ ቁጥሩ እየበዛ የመጣውን የተፈናቃዮች ችግር እልባት ለመስጠት የሚያስችል የሕግ ማዕቀፍም ሆነ ሥራውን በባለቤትነት የሚሠራ ተቋም እንደሌላት ተነገረ፡፡ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ረዕቡ ግንቦት 3 ቀን 2014 ዓ.ም. ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአሥር ወራት ሥራ አፈጻጸም ሪፖርቱን ሲያቀርብ፣ አገሪቱ ከተፈናቃዮች ጋር የተያያዙ ችግሮችን ለመፍታት የሕግም ሆነ የተቋምም ማዕቀፍ እንደሌላት ተመልክቷል፡፡ በየጊዜው በግጭትና ጦርነት ቁጥራቸው እየጨመረ የመጣውን የተፈናቃይ ዜጎችን ችግር መፍታት ባለመቻሉ ብዙዎች ለረዥምና ውስብስብ ችግሮች ተዳርገዋል ተብሏል፡፡ በየጊዜው ከተፈናቃዮች አያያዝ ጋር በተገናኘ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት ቅሬታ ቢቀርብም፣ የነዚህን ዜጎች ጉዳይ የሚመለከት ተቋምም ሆነ ሕግ ባለመኖሩ ችግሩን ለመፍታት አለመቻሉን ነው የኮሚሽኑ ሪፖርት ያመለከተው፡፡
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ ለሕግ፣ ፍትሕና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ባቀረቡት ሪፖርት አሳሳቢና መሻሻል የሚሏቸውን ጉዳዮች አስቀምጠዋል፡፡
በጦርነትና ግጭት ውስጥ ባሉ አካባቢዎች ተከታታይ ክትትል ማድረግን በተመለከተ ችግር መኖሩን ያመለከቱት ኮሚሽነሩ ‹‹በብሔር፣ በሃይማኖትና በአስተዳደር ወሰን በሚነሱ ግጭቶች ከፍተኛ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት ደርሷል፤›› ሲሉ ተናግረዋል፡፡ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን የማስቆም ዋና ሚና የመንግሥት መሆኑን በማስገንዘብም ሁኔታዎች ወደነበሩበት ሰላማዊ ሁኔታ እንዲመለሱ ጥብቅ ክትትልና ድጋፍ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡ መፈናቀልን በተመለከተ ‹‹ዘላቂ የሆነ መፍትሔ ያጡና ለረዥም ጊዜ የተፈናቀሉ ዜጎች በመብዛታቸው አግባብነት ያለው ጥበቃና ድጋፍ ለመስጠት በቂ ትኩረት ተሰጥቶት የሕግ ማዕቀፍና ተቋም መፍጠር፤›› አስፈላጊ መሆኑን አመልክተዋል፡፡
ተጠያቂነትና የሕግ የበላይነትን በሚመለከት ደግሞ የመንግሥት ኃይሎች የሚፈጽሙት ከሕግ ውጪ የሆነ ግድያ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን ኮሚሽነር ዳንኤል (ዶ/ር) ገልጸዋል፡፡
ኮሚሽነሩ ከዚሁ ጋር በተያያዘ በአሳሳቢነት ካነሷቸው ጉዳዮች መካከል የመንግሥት ኃይሎች የሚወስዱት ያልተመጣጠነ ኃይል፣ ያለፍርድ ቤት ትዕዛዝ ማሰርና በእስር ማቆየት፣ በጋዜጠኞችና ማኅበረሰብ አንቂዎች ላይ የሚፈጸም ተደጋጋሚ እስራት፣ እንዲሁም ብሔር ተኮር እስራት ለሰብዓዊ መብት ጥሰቶች አጋላጭና ዕርማት የሚያስፈልጋቸው መሆኑን ገልጸዋል፡፡
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ራኬብ መሰለ በበኩላቸው የተቋሙን ውጤታማ ሥራዎችና ተቋማዊ ፈተናዎች በሰፊው ዘርዝረዋል፡፡ ክትትልና ምርመራን በተመለከተ በዘጠኝ ወራት 1,410 አቤቱታዎች አስተናግደናል፣ 65 ቦታዎችን ሸፍነናል፣ ከ700 ያላነሱ ቃለ መጠይቆችን አድርገናል እንዲሁም 450 ሺሕ ስደተኞች የያዙ አሥር የስደተኞች መጠለያ ጣቢያዎች ላይ ክትትል አድርገናል ሲሉ ለምክር ቤቱ አስረድተዋል፡፡
ኮሚሽነር ራኬብ አክለውም ከ270 ባላነሱ ፖሊስ ጣቢያና ማረሚያ ቤቶች ላይ ክትትል መደረጉን የጠቀሱ ሲሆን፣ ወደ 750 አላግባብ የታሰሩ ሰዎችን ማስፈታታቸውንም አስረድተዋል፡፡ በአጠቃላይ በአሥር ወራት ‹‹ወደ 40 የክትትል ውጤቶችን በመግለጫም ሆነ በሪፖርት መልክ ይፋ አድርገናል፤›› ያሉት ኮሚሽነሯ ነገር ግን በተፈናቃዮች ጉዳይ ላይ ያለው የሕግና የተቋም አልባነት ለሥራቸው ፈተና እንደሆነ ለምክር ቤቱ ተናግረዋል፡፡
‹‹ወደ 1.5 ሚሊዮን የአገር ውስጥ ተፈናቃዮችን የሚያስጠልሉ 47 ጊዜያዊ መጠለያ ጣቢያዎችን በአምስት ክልሎች ክትትል አድርገናል፤›› ያሉት ኮሚሽነር ራኬብ ‹‹ሆኖም የተፈናቃዮችን ቅሬታ የሚሰማና ችግሮችን የሚፈታ ተቋም በአገሪቱ አለመኖሩ ችግር ፈጥሯል፤›› ብለዋል፡፡
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ለፓርላማው የሕግ፣ ፍትሕና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ባቀረበው የአፈጻጸም ሪፖርት፣ በኢትዮጵያ የተፈናቃዮችን ጉዳይ የተመለከተ ራሱን የቻለ ሕግና ተቋም እንዲበጅ ጠይቋል፡፡ ኢሰመኮ ከዚህ በተጨማሪም ሥራውን ለማስፋትና ቅርንጫፎቹን ለማብዛት እንዲረዳው ተጨማሪ በጀት ምክር ቤቱ እንዲፈቅድለት ለቋሚ ኮሚቴው ጥያቄ አቅርቧል፡፡
by Dawit Atreso
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ የነበረችው ፅጌሬዳ ግርማይን በመግደል የተከሰሰው ተማሪ ለውሳኔ ለግንቦት 19/2014 ዓ.ም ተቀጥሯል።
ተከሳሹ የመከላከያ ምስክሮች በማቅረብ ራሱን ሲከላከል ቆይቷል።
ፍርድ ቤት የቀረቡ ምስክሮች "ሟች እና ተከሳሾች ጓደኛሞች እንደነበሩ እንደሚያውቁና ከዚያ ውጪ የሚያውቁት ነገር እንደሌለ" ገልጸዋል።
በሕግ ጥላ ስር ሚገኘው ተከሳሽ ብሩክ በላይነህ ላይ የፍርድ ማቅለያ እና ማክበጃ መቅረቡን የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የሕግ አገልግሎት ዳይሬክተር አቶ መርኪያ መንገሻ ተናግረዋል።
ተከሳሹ በአርባ ምንጭ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጉዳዩን እየተከታተለ ይገኛል።
ፍርድ ቤቱ ቤቱ ውሳኔ ለመስጠት ተለወጫ ቀጠሮ ለግንቦት 19/2014 ዓ.ም ሰጥቷል።
ጥር 23/2014 ዓ.ም የተገደለችው የ20 ዓመቷ ተማሪ ፅጌሬዳ ግርማይ በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የሆቴልና ቱሪዝም ማኔጅመንት የ2ኛ ዓመት ተማሪ ነበረች፡፡