ጋዜጠኛ አልዓዛር ተረፈ ታሰረ

 ethiopian human right commussion

የ "አል አይን ኒውስ" የኢትዮጵያ ዘጋቢ መታሰሩ

14 July 2022

የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች መገናኛ ብዙሃን ለሆነው " አል አይን ኒውስ " በዘጋቢነት የሚሰራው ጋዜጠኛ አልዓዛር ተረፈ ዛሬ ሐሙስ ሐምሌ 7 ከሰዓት ሲቪል በለበሱ ጸጥታ ኃይሎች መያዙን ባለቤቱ እና ባልደረባው ገልፀዋል።

ጋዜጠኛው በጸጥታ አካላት ከተያዘ በኋላ በአዲስ አበባ ላምበረት አካባቢ ወደሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ መወሰዱን አመልክተዋል።

አልዓዛርን በታሰረበት ፖሊስ ጣቢያ በመሄድ የጎበኘው ባልደረባው ዳዊት በጋሻው፤ ጋዜጠኛው የተያዘው ላምበረት መናኸሪያ አካባቢ ከሚገኝ ካፌ እንደሆነ ገልጿል።

የሲቪል ልብስ የለበሱ ሁለት ግለሰቦች ጋዜጠኛውን መታወቂያ እንዲያሳያቸው እንደጠየቁት እና " እንፈልግሃለን " ብለው እንደወሰዱት የዓይን እማኞች ነግረውኛል ብሏል።

ሁለቱ ግለሰቦች አልዓዛርን በያዙበት ወቅት " ለችግኝ ተከላ ጥሩ አመለካከት የለህም፤ ‘ቤተ መንግስት ገብተን፤ በደም የበቀለውን ችግኝ እንነቅላለን’ ብለሃል " በሚል ሲወነጅሉት መሰማታቸውን ጋዜጠኛ ዳዊት ተናግሯል