by Dawit Atreso
ከሰሞኑን የኤሌክትሮኒክ ትራንስፖርት የሚሰጡ ወገኖች ላይ እየደረሰ ያለው የተቀናጀ ወንጀል እየተስፋፋ ይገኛል። በተለይም በከተማዋ ከመንግስት ጋር በተያያዘ የሚገቡ ከተለያዩ ክፍለ ሃገሮች የሚመጡ ውንጀለኞች ተስፋፍተዋል።
ባለፈው አርብ ምሽት አንድ ወንድማችን ከፍየል ቤት ወደ 22 ከመንገድ ላይ ሰው ጭኖ አውራሪስ አካባቢ ሲደርስ አንገቱን አንቀው እራሱን እንዲስት በማድረግ ከመኪናው አሰወጥተው በመወርወር መኪናውን ይዘው መሰወራቸውን ይታወሳል።
የአሁኑ ግን ከዝርፈያም ባለፈ የሰው ህይወት የተቀጠፈበት ነው። የአሁኑ ግን ከዝርፈያም ባለፈ የሰው ህይወት የተቀጠፈበት ነው። ከላይ በፎቶ የምትመለከቱ ሳላዲን ሐሰን ይባላል። የምትመለከቷት መኪናም የእሱ ነበረች።
ትናንት ከቀኑ 10:00 ሰዓት ላይ እጅግ በጣም አሳዛኝ በሆነ ሁኔታ ተገድሎ መኪናው ተዘርፏል። ሳላዲን የራሱን እና የቤተሰቦቹን ኑሮ ለማሻሻል ሲል ይተዳደርበት በነበረው የመኪና እጥበት ስራ ከሚያገኘው ገቢ በመቆጠብ ነው መኪናዋን ገዝቷት የነበረው። ሳላዲን በጩቤ ተወግቶ ተገድሎ መኪናው ከመዘረፉ በፊት የመጨረሻ አገልግሎት ለመስጠት የተደወለበት አካባቢ ገርጂ 24 ልዩ ቦታ ኤርትራ ቆንጽላ ጽ/ቤት አካባቢ መሆኑን የሚሰራበት ድርጅት እንደነገራቸው ጓደኞቹ ገልፀዋል። ቤተሰቦቹ ከባድ በሆነ መሪር ሀዘን ውስጥ የሚገኙ ሲሆን ጓደኞቹም በተፈጠረው ሁኔታ እጅግ መደናገጣቸውንና ከባድ ሀዘን ውስጥ ናቸው።