ህግ-1 : ከአለቃህ በልጠህ ለመታየት አትሞክር ("Never Outshine The Master")

#
31 July 2022

by Dawit Atreso

ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ ልክ እንደ ክርስቲያኖቹ መጽሐፍ ቅዱስ እና እንደ እስላሞቹ ቁርዓን ተጠንቅቆ የሚያከበረውና የሚፈጽመውን እንደ መለኮታዊ መገለጥም የሚቆጥረውንና የህይወቱም የዕለት ተዕለት መመሪያው አድርጎ ስለሚመራበት 48 የስልጣን ህጎች ተፃፈ በሮበርት ግሪን ።

ይህ ደራሲ በዜግነት አሜሪካዊ ሲሆን እንደ ፈረንጆቹ ዘመን አቆጣጠር ግንቦት 1959 ተወለደ ። ደራሲው በስትራቴጂ፣ በኃይል እና በማታለል ጥበብ ላይ አስገራሚ መጻሕፍት የጻፈም ደራሲ ነው። ደራሲው እስከ አሁን 6 ያህል ዓለም አቀፍ ምርጥ የሽያጭ ገቢዎችን ያተረፉ መጻሕፍትን ጽፏል።

  • The 48 Laws of Power (48ቱ የኃይል ሕጎች)
  • The Art of Seduction (የማሳሳት ጥበብ)
  • The 33 Strategies of War (33ቱ የጦርነት ስልቶች)
  • The 50th Law (with rapper 50 Cent) (50ኛው ሕግ ከራፐር 50 ሴንት ጋር)
  • Mastery, and The Laws of Human Nature (ጌትነት እና የሰው ልጅ የተፈጥሮ ሕጎች) ናቸው ።
  • ታድያ ይህ መፅህፍ እንዲ ያሳስባል ምቹ ጊዜ እስክታገኝ እና ልቡ ድረስ ኀዘን እንዲሰማው አድርገህ እስክታስወግደው ድረስ አለቃህን ከአንተ በላይ እነደሆነ፣ የበላይነትም እንዲሰማው አድርግ። ደኅንነቱ የተጠበቀ እንዲመስለውና እንዲዘናጋ ከፈለግክ ችሎታህን ከልክ በላይ አታሳየው። ከኋላው ሆነህ እሱን ከፊት እያስቀደምክ መቼ እንደምታስወግደው አስላ ።