by Dawit Atreso
ወጣቱ ገጣሚ በላይ በቀለ ወያ እስካሁን ያለበት አለመታወቁ እንዳሳሰባቸው ቤተሰቦቹ ገልጸዋል። ገጣሚ በላይ በ ሰኔ 21 ቀን 2014 ከቀኑ በ 8 ሰዓት ፈረንሳይ ሌጋሲዮን ከሚገኘው ጊዮርጊስ ምግብ ቤት ትፈለጋለህ ተብሎ እንደተወሰደ እህቱ ሰላም በቀለ ወያ ትናገራለጭ ። ማክሰኞ እለት ሰሌዳ በሌላቸው ተሽከርካሪዎች ውስጥ በነበሩ እና ማንነታቸው በማይታወቅ ሲቪል በለበሱ የጸጥታ አካላት ነን ባዮች መወሰዱን ያስረዳችው እህቱ ሰላም በፌደራል እና በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ቢሮ እንደዚሁም በየካ ክፍለከተማ ውስጥ በሚገኘው ፖሊስ ጣቢያ ውስጥ ብንጠይቅም አድራአሻው ሊታወቅ አልቻለም ስትል በማህበራዊ ሚዲያ ባስተላለፈችው መልዕክት ተናግራለች ።
እናቱ እና አባቱ በድንጋጤ መታመማቸውን የገለፀችው ሰላም እናቱ ፅጌ ገብረ እግዚአብሄር ልጄ የት ነው ያለው በማለት ሀገር እና ህዝብን መጠየቃቸውን ተናግራለች ። በመጨረሻም የወንድሟን ድምጽ ከሰማች ሶስት ቀን ማለፉን እንደዚሁም ያለበት አለመታወቁን እና መላ ቤተሰቡን ለቀፍተኛ ጭንቀት መዳረጉን ተናግራለች ።
በተደጋጋሚ ሰዎችን ስልታዊ በሆነ መልኩ ማፈን እና መሰወር በአለም አቀፍ ደረጃ በሰዎች ስብእና ላይ ወይም crime against humanity ነው። አፍኖ መሰወርን ለመከላከል ሲባል በ1992 በወጣው ድንጋጌ ሠዎችን ከፈቃዳቸው ውጭ አስገድዶ በማሰር መሰወር ወይም ያሉበትን ቦታ እንዳይታወቅ በማድረግ በአንድ ማህበረሰብ ውስጥ ለህግ የበላይነት እና ለሰብአዊ መብቶች መከበር በቂ ትኩረት እንዲያገኙ እና የዚህ አይነቱ ግልጽ አፈና እና መሰወር በሰዎች ስብእና ላይ ተነጣጥሮ የሚፈጽም ስለሆነ የሚከላከል ዓለም አቀፍ ህግ ነው።
ይሄ አፈና አለም አቀፍ ህጎችን የሚፃረር እና በፍጥነት የታፈኑ ጋዜጠኞች ፣ ምንም ያላጠፉ የባልደራስ እና የፋኖ አመራሮች እና ደጋፊዎች ፣ የትግራይ ተወላጆች ይፈቱ!!!!