በጋዜጣዉ voice|ET News by Dawit Atreso
የትግራይ ፕሬዝዳንት ዶ /ር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል በኢትዮጵያ መንግስት እና በትግራይ ክልል መካከል ስለሚኖረው የሰላማዊ ውይይት ሂደትን በተመለከተ ለአፍሪካ ህብረት፣ለኬንያው ፕሬዝዳንት፣ለአውሮፓ ህብረት፣ለተባበሩት አረብ ኤምሬትስ እና ለታንዛንያው ፕሬዝዳንት በጻፉት ግልጽ ደብዳቤ የትግራይን መንግስት አቋም አሳውቀዋል። በዚህም መስረት ለሰላም ሲባል የሚደረገው ድርድር መሰረታዊ የሰብአዊ መብቶችን፣ የዲሞክራሲ እና የተጠያቂነት መርሆዎችን ያጣጣመ ከሆነ ለመደራደር ዝግጁ ነን ያሉ ሲሆን ከዚህ ውጭ ምስጢራዊ ስምምነቶችን ለማድረግም ሆነ መሰረታዊ መርሆቻችን የጣሰ ድርድር ለማድረግ ፍላጎት የለንም ብለዋል።
ከዚህ ቀደም በተለያዩ ጊዜያት ከ አፋኙ መንግስት ጋር ድርድር ላይ ከነበሩ ለተጠየቁት ጥያቄ ፕሬዘዳንቱ ምንም አይነት ድርድር ላይ እንዳልነበሩ ገልፀዋል።