በጋዜጣዉ voice|ET News by Dawit Atreso
"…የኦፌኮው ምክትል ሊቀ መንበር ሃጂ ጀዋር መሀመድ 30k ተመልካች በነበረው ከአቡንቱ ዩቲዩብ ቻናል ጋር ያደረገውን ቃለ መጠይቅ ደግሜ አየሁት። የጃዋር እርጋታው፣ ጥንቃቄው፣ የድምጽ ቶኑ ዝግታ፣ መወራጨት፣ መጮሁ፣ መሳለቁ፣ ማሳቀቁ፣ ማላገጡ፣ መተንኮስ ማንጓጠጡ ሁሉ ቀርቶ እንዲህ ጭጭት ብሎ ሰውነቱ ትንሽ ከስቶ፣ ፀጉሩም ሸብቶ፣ ለሃገር ሰላም ሁሉም ይጸልይ የሚል ሐዋርያ መስሎ መታየቱን ታዝቤአለሁ። እስር እንዲህ የሚያርቅ ከሆነ እስር ለዘላለም ይኑር። ትንሽ ቢቆይ ደበበ እሸቱን ወይም አንዷለም አራጌን ይሆን ነበር የሚሉም ሰዎች ተደምጠዋል። ፐ እርጋታ…!
"…ከወር በፊት በኦፌኮ በፖለቲካ ድርጅቱ በኩል " ጽንፈኛ" ብሎ የከሰሰውን ፋኖንም በተመለከተ አሁን የሰነዘራቸው መልእክቶች ሰማይና ምድር ሆኖ አግኝቻለሁ። በዚህ አጭር ጊዜ ውስጥ የፋኖ አዛኝ፣ የዐማራን ብሔርተኝነት መጦዝና፣ መመንጠቅ እንደሚያሳስበው ሆኖ መቅረቡም ገርሞኛል።
"…ጃዋር በዚህ ቃለ መጠይቁ የዐማራ ፖለቲካ የማይታመንና ፈጣን የሆን የለውጥ ሁኔታ ውስጥ መግባቱን፣ ብሔርተኝነቱም ፈጣን የሆነ እድገት ማሳየቱን፣ በተለይ የፌደራል መንግሥቱ ከህወሓት ጋር በነበረው ጦርነት ወቅት የዐማራን ድጋፍ መፈለጉን ተከትሎ ዐማራን በሙሉ ወታደር ማድረጉን፣ መሳሪያ ማርክና ታጠቅ ብሎም ሁሉም በአንዳፍ ብሎ መታጠቁን ሳይደብቅ መስክሯል። እንዲህ ካልከው በኋላ መልሰህ በኃይል መሳሪያህን እገፍሃለሁ መባሉ አደጋ መሆኑን በሰከነ መንፈስ ሲናገር ተደምጧል።
"…የፌደራል መንሥቱ ከህወሓት ጋር ሲደራደር ዐማራን በድርድሩ አለመሳተፉ፣ የመገለልና የመገፋት ስሜት መፈጠሩን፣ ለጦርነቱ ሕይወቱን እንዲገብር ጠርተኸው፣ የማረከውን መሳሪያ ለግልህ ውስድ ብለኸው ስታበቃ መልሰህ የድርድሩ ተሳታፊ ሳታደርገው ውሰድ ያልከውንም ትጥቅ በጉልበት ፍታ ማለቱ ከባድ አደጋ እንዳለውም ጃዋር በለሆሳስ ምክር ሲሰጥ ታይቷል።
"…ፋኖ ላይ የሰላ ትችት ማድረግ ይቻላል ይላል ጃዋር። (እሱ በድርጅቱ በኩል ጽንፈኛው ፋኖ ሲል እንደነበረው ማለት ነው) ነገር ግን ፋኖን በማግለልና በማሳደድ አክራሪወች ቢኖሩም እንኳ እደመስሳቸዋለሁ፣ አወድማቸዋለሁ በሚል መንግሥታዊ ጉልበተኛ አስተሳሰብ አይደለም ብሏል። ፋኖነትን ለጊዜው እናስተፍሰው ይሆናል ነገር ግን የፋኖነትን ስሜት ይበልጥ ታሳድገዋለህ እንጂ በዚህ መልኩ ልታሸንፈው አትችልም ነው ያለው ጃዋር። ( ህወሓት ዱላ፣ በትር ሳይቀር በእጁ እንዳይዝ አድርጋ ረግጣ የያዘችውን ዐማራ በዐዋጅ ታጠቅ ካልከው በኋላ ድንገት መጥተህ ፍታ ስትለው አደጋ አለው የሚል ነው የሚመስለው ጃዌ)
"…እርግጥ ነው መንግሥት በፋኖ ላይ የወሰደው አሳፋሪ ተግባር መልሶ እየለበለበው ነው። ከወር በፊት ጽንፈኛው ፋኖ እርምጃ ይወሰድበት እያለ መንግሥትን ሲማጸን፣ ሲገፋ የነበረው ጃዋርስ ምን ዓይነት ራዕይ ታይቶት ነው ይሄ ነገር አደገኛ ነው ይቁም ወደሚል ድንገቴ ሰበካ የወረደው። ፋኖ የገደለው ሰውም፣ የዘረፈውም ባንክ እንደሌለ እየታወቀ ስሙ ሲያጠለሹ ከከረሙ በኋላ አሁን ደርሰው አዛኝ መስለው መከሰታቸው ጥያቄ ይጭራል።
"…እኔ ግን እላለሁ ዐማራ አሁንም በሰበካ፣ በኢትዮጵያ ሱሴ ዲስኩር ለዳግም ንቀት፣ ለዳግም ሞትና ስደት እንዳትዳረግ፣ እንደ ዜጋ እንድትታይ፣ እንድትከበር ፋኖነትህን አጥብቅ። የሰላምን በር አትዝጋ፣ ግን ባዶ እጅህን አይሁን። ሰዎቹ የሚታመኑ አይደሉምና እየተፈራረቁ በተበረጠቁ ቁጥር አጀንዳህን አትቀይር። ጃዋር ግን ሲታይ እንደለማ መገርሳ፣ እንደ ዐቢይ አሕመድ ሲመሽ ካላደፈረሰው በቀር ለአሁኑ ሲታይ እጅግ ያደገ፣ የተረጋጋ፣ እንደ አረጋዊ የሰከነ መስሎ ለመተወን ሞክሯል።
"…የአሜሪካንን ፓስፖርት ከማግኘት 3 ወር ነው የፈጀብኝ፣ የኢትዮጵያ ፓስፖርት ለማግኘት 2 ዓመት እንደፈጀበት የተናገረው ስሰማ ግን የኢትዮጵያዊነትን ክቡርነትና ውድ ማንነት ሲመሰክር ማየቴን አልደብቅም። ኢትዮጵያ የናቋት፣ የሰደቧት፣ የረገሟት፣ ሰድበውም ለሰዳቢ አሳልፈው የሰጧት ኃይሎች በሙሉ እግሯ ላይ ይወድቃሉ።
"…ፋኖም ዐማራም አጀንዳችሁን አትቀይሩ…!!