@bbc amharic
ሮይተርስ ዛሬ ይዞት በወጣው ዘገባ ባለፈው ሳምንት የመጨረሻ ቀናት ላይ የኤርትራ ጦር በሽራሮ ከተማ ላይ በከፈተው ጥቃት አንዲት የ14 ዓመት ታዳጊ መገደሏን እና 18 ሰዎች ደግሞ መቁሰላቸውን አመልክቷል። ሮይተርስ ፤ ከሰብዓዊ ድርጅት ተቋማት የተገኘ መረጃ የሰፈረበት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (UN) ሰነድ መመልከቱን በመግለፅ ነው ዘገባውን ይዞ የወጣው። በዚህም የኤርትራ ጦር ቢያንስ 23 ጊዜ ወደ ሽራሮ ከባድ መሳሪያ ተኩሷል። ባለፈው ቅዳሜ እና እሁድ ግንቦት 20 እና 21 ቀን 2014 ዓ.ም. የኤርትራ ሠራዊት በሽራሮ ከተማ ላይ ከፍቶት ነበረ በተባለው ጥቃት፣ ከቀያቸው የተፈናቀሉ ሰዎች ተጠልለውበት የነበረ #ትምህር_ቤት ጉዳት ደርሶበታል። የከባድ መሳሪያ ጥቃት ተፈጽሞባታል የተባለችው ሽራሮ ከኤርትራ ድንበር 11 ኪሎ ሜትር አካባቢ ርቀት ላይ የምትገኝ ናት።