by Dawit Atreso
በዛሬው እለት ሱዳን ኢትዮጵያን በግልፅ መውረር ጀምራለች፤ ባትጀምር ይግርመኝ ነበር። አይ ኢትዮጵያ! የአራት ኪሎው ተረኛው መንግስት አሁን ላይ በተለይም የኢትዮጵያን ህዝብ ለማደንዘዝ እና አጀንዳ ለማስቀየር የተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ሌት ተቀን በመስራት ላይ ይገኛል። ይንንም ተከትሎ በወልጋ ሆን ብሎ ያስጨፈጨፋቸውን ከሁለት ሺህ በላይ ንፁሃን አማርኛ ተናጋሪ ከህጻን እስከ አዋቂ ነፍሶችን፤ አሁን ደግሞ በሱዳን እና በደቡብ ሱዳን ተወረናል ድረሱልን እያለ ይገኛል። ግልጹን እንነጋገር ከተባለ የዘሪፖርተር ጋዜጣ በአዲሱ በደቡብ ምዕራብ ክልል የደቡብ ሱዳን ታጣቂዎች ከመቶ ሃምሳ በላይ ኪሎ ሜትር በላይ መሬት መውረራችውን ገልጾ ሲያበቃ በሰአታት ውስጥ ከዌብሳይቱ ላይ ዘገባውን እንዲያወርድ ተደርጓል። አይ አፋኙ !!
የሱዳን መንግስትና የአፋኙ የእትዮጵያ መንግስት ጦርነት እየጎሰሙ የሚገኙበት ሁኔታ ነው ያለው። በዚህም የሱዳኑ መሪ አልቡርሃን የሃገሩን ህዝብ አጀንዳ ለማስቀየር እና ካለበት ተቃውሞ ራሱን ለማዳን በማለት የጦርነት ጉሰማ ላይ ይገኛል። በአንፃሩ ለኢትዮጵያው መንግስት የተመችው ሁኔታ ተፈጥሮለታል። የንፁሃን ደም በከንቱ እየፈሰሰ እና ሰብአዊ መብት እና በአንድ ሃገር ላይ አንደኛ ዜጋ እና ሁለተኛ ዜጋ ሆኖ በተከፋፈለበት ሁኔታ አሁን ድጋሚ ወደ ጦርነት ለመግባት የሚደረግ ጉሰማ ተገቢ ኣይደለም።
በምዕራብ ጎንደር ዞን የምዕራብ አርማጨሆ ወረዳ አስተዳዳሪ የሆኑት አቶ ደሳለኝ አያና ለቢቢሲ አማርኛ አገልግሎት የሰጡት ቃል ፦
- የሱዳን ሠራዊት በኢትዮጵያ በኩል ያሉ የድንበር አካባቢዎችን በከባድ መሳሪያ ደብድቧል። ድብደባው ለቀናት የዘለቀ ነው። እስከ ትላንት ማክሰኞ ከሰዓት ድረስ ሲደበድቡ ነበር።
- ነዋሪዎች ግጭቱ ሊባባስ ይችላል የሚል ስጋት አላቸው። አንዳንዶችም በአቅራቢያ ወዳሉ አካባቢዎች የመሄድ ሃሳብ አላቸው።
- ባለፉት ሶስት ቀናት በተፈጸመው የከባድ መሳሪያ ጥቃት #በሰው_ላይ_ጉዳት_አልደረሰም። የከባድ መሳሪያዎቹ በእርሻ ቦታዎችና የግብርና ካምፖች ላይ ጉዳት አድርሰዋል።
- በሱዳን የከባድ መሳሪያ ጥቃት ምክንያት ነዋሪዎች ባለፉት ቀናት በእርሻ ማሳቸው ላይ የተለመደውን የዕለት ከዕለት ሥራቸውን ከማከናወን ተቆጥበዋል።
- የንግድና የሥራ እንቅስቃሴ ተስተጓግሏል። ሱዳንና ኢትዮጵያ የሚገናኙበት የድንበር ከተማ የሆነችው የገለባት መተላለፊያ #ተዘግቷል።